ዋና ገጽ| ምርቶቻችን| ስለ አበባ ባልትና| አድራሻችን|

   በባልትና ምርት አዘጋጅነት አገልግሎት መስጠት ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ለደንበኞቻችን ጥራትና ደረጃቸዉን የጠበቁ የባልትና ምርቶችን ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ ከተዘጋጁና ከታሸጉ ምርቶቻችን በተጨማሪ ጥሬ ምርቶችን ለደንበኞቻችን እናቀርባለን፡፡ ምርቶቻችን ባህላዊዉን የአዘገጃጀት ሂደት ሳይለቁ የቤት ጣእማቸዉን አንደጠበቁ የሚዘጋጁ ናቸዉ፡፡


በርበሬ
በርበሬ በ ኢትዮጵያዉያን አመጋገብ ትልቅ ቦታ ይይዛል፡፡ የተቀመመ በርበሬ ጣዕሙ የተስተካከለ እንዲሆን የሚጨመሩበት ቅመማ ቅመሞች ጥራትና ብዛት ወሳኝ ነወ፡፡ የአበባ ባልትና በርበሬ የሚከተሉትን ቅመማት በዉስጡ ይይዛል፡
 • አንደኛ ደረጃ የማረቆ በርበሬ
 • ኮረሪማ
 • ጥቁር አዝሙድ
 • ነጭ ሽንኩርት
 • ቀይ ሽንኩርት
 • ድንብላል
 • ጦስኝ
 • ቅርንፉድ
 • ቀረፋ
 • ጥምዝ
 • አዝመሪኖ
 • ገዉዝ
 • ጤና አዳም
 • ዝንጅብል
 • ኮሰረት
 • ነጭ አዝሙድ

    ከተቀመመ በርበሬ በተጨማሪ ያልተቀመመ ንፁህ በርበሬ እናቀርባለን፡፡

አጃ
አጃ አጥሚት ለመስራት አስፈላጊ የሆነ የባልትና ምርት ነዉ፡፡ በተለየ መልኩም አጃ ለገንፎና ለመሰል ምግቦች ዝግጅት አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡፡
 • አጃ
 • የአጃ ገብስ
 • ቀይ ጤፍ
 • አብሽ
 • ዘንጋዳ
 • ባቄላ
 • ምስር ክክ
 •  

ቡላ
ቡላ ከ እንሰት ተክል የሚገኝ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉ የምግብ አይነት ነዉ፡፡
 • ንፁህ ቡላምጥን ሽሮ
ሽሮ በኢትዮጵያ እንዲሁም በተቀረዉ የአለም ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ ተቀባይነት እያገኘ ያለ ምግብ ነዉ፡፡ ለሁሉም ምርቶቻችን ከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ የምንሰጥ ቢሆንም ለሽሮ የሞናደርገዉ ጥንቃቄ የተለየ ነዉ፡፡
 • አተር ሽሮ
 • ኮረሪማ
 • ጥቁር አዝሙድ
 • ነጭ ሽንኩርት
 • ቀይ ሽንኩርት
 • በርበሬ
 • በሶብላ
 • ዝንጅብል
 • ጨዉ
 • የተቆላ አብሽ
 • ሮዝመሪኖ
 • ነጭ አዝሙድ

 ከላይ የተዘረዘሩት ቅመማ ቅመሞች ከአተር ጋር ከተቀላቀሉ በኃላ ቅልቅሉ እንዲደርቅ ይደረጋል፡፡ ከደረቀ በኃላ በአግባቡ ይፈጭና በወጥ ወይም በሌላ መልክ ለምግብነት መዘጋጀት ይችላል፡፡
መከለሻ
መከለሻ የተለያዩ ቅመማትን አንድ ላይ ቀላቅሎ በመዉቀጥ የሚሰራ የምግብ ማጣፈጫ ነዉ፡፡ የተወሰኑት ቅመማት ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡
 • ቀረፋ
 • ኮረሪማ
 • ጥቁር አዝሙድ
 • ቁንዶ በርበሬ

 ከላይ ከተዘረዘሩት ቅመማ ቅመሞች በተጨማሪ በማንኛዉም የሽያጭ ሱቅና ሱፐር ማርኬት ሊያገኟችዉ የሚችሉ ከ ሰላሳ በላይ ምርቶች አሉን፡፡ ዛላ በርበሬ፣ አተር፣ የበቆሎ ዱቄት እና ሌሎችም ያልተዘጋጁ ምርቶችን ከፈለጉ ያነጋግሩን፡፡

ኮፒ ራይት@2012 አበባ ባልትና፣
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ!
webmaster@abebabaltena.com.et