ዋና ገጽ| ምርቶቻችን| ስለ አበባ ባልትና| አድራሻችን|

ታሪክ

       አበባ ባልትና በ 2001 ዓ.ም በግል ድርጅትነት ተመዝግቦ ስራ የጀመረ ሲሆን ወ/ሮ ፎዚያ ገለቱ በመስራችነት፣ አቶ ሸረፋ አህመዲን ደግሞ ድርጅቱ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በስራ አስኪያጅነት ድርጅቱን እያስተዳደሩ ይገኛሉ፡፡ ድርጅታችን ከምስረታዉ አንስቶ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ካለዉ ፅኑ ፍላጎት በመነሳት ደንበኞችን መሰረት ያደረገ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የሰዉ ሃይል

       ማንኛዉም አይነት የምግብ ዝግጅት ስራ ባለሙያ እንደሚፈልግ አያጠያይቅም፡፡ አበባ ባልትና በሙያቸዉ የበቁና ታታሪ ሰራተኞችን የያዘ ድርጅት ሲሆን፣ ከምርት ጀምሮ እስከ ትራንስፖርት እንዲሁም ሽያጭ ድረስ ያሉትን ስራዎች በአግባቡ መወጣት የሚችሉ ሰራተኞች መናኸሪያ ነዉ፡፡ ላለፉት አመታት የምርት ጥራት ቁጥጥር በማድረግ የምርት ሂደቱን ስትመራ የቆየችዉ ወ/ሮ መሰረት ክንፈ የተባለች ባለሙያችን ነች፡፡ በዚህ ሰዓት ከ አርባ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች በድርጅታችን ዉስጥ በቋሚነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

አደረጃጀት

       ከላይ እንደተገለፀዉ አበባ ባልትና በ ወ/ሮ ፎዚያ ገለቱ ከተመሰረተ በኃላ በአቶ ሸረፋ አህመዲን ስራ አስኪያጅነት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በእያንዳንዱ የምርት ጣቢያ የጥራት ቁጥጥር የሚያካሂዱ ባለሙያዎች የሚገኙ ሲሆን በተለያየ ስፍራ የሚገኙት የመሸጫ ሱቆቻችን ደንበኞቻችንን በቅርብ ለማግኘት አስችለዉናል፡፡

ደንበኞቻችን

       ከምርቶቻችን ጥራትና ከአገልግሎታችን አርኪነት የተነሳ የደንበኞቻችን ብዛት በየቀኑ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ባለፉት አመታት ያለማሰለስ የደረግነዉ ጥረት ተሳክቶ በአሁኑ ሰዓት ለከፍተኛ የመንግስት እና የግል ተቋማት ምርቶቻችንን ለመቅረብ የሚያስችለንን አቅም ገንብተናል፡፡ ከደንበኞቻችን መካከል ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ሙገር ሲሚንቶ የሚገኙበት ሲሆን፣ ካፌዎች፣ ሆቴሎች እና ግለሰቦች ይገኙበታል፡፡ ከዚህ በኃላ እርስዎም የተከበሩ ደንበኛችን እንደሚሆኑ አንጠራጠርም፡፡

ለጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን!

ኮፒ ራይት@2012 አበባ ባልትና፣
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ!
webmaster@abebabaltena.com.et